ኢዮብ 38:39-41

ኢዮብ 38:39-41 NASV

“ለአንበሳዪቱ ዐድነህ ግዳይ ታመጣለህን? የተራቡ የአንበሳ ግልገሎችንስ ታጠግባለህን? እነርሱ በዋሻ ውስጥ ያደባሉ፤ በደን ውስጥም ይጋደማሉ። ልጆቿ ወደ እግዚአብሔር ሲጮኹ፣ ምግብ ዐጥተው ሲንከራተቱ፣ ለቍራ መብልን የሚሰጥ ማን ነው?