ኢዮብ 2:7-10

ኢዮብ 2:7-10 NASV

ከዚህ በኋላ ሰይጣን ከእግዚአብሔር ፊት ወጥቶ ሄደ፤ ኢዮብንም ከእግር ጥፍሩ እስከ ራስ ጠጕሩ በክፉ ቍስል መታው። ኢዮብም ገላውን ለማከክ ገል ወሰደ፤ በዐመድም ላይ ተቀመጠ። ሚስቱም፣ “አሁንም ታማኝነትህን አልተውህምን? ይልቁን እግዚአብሔርን ርገምና ሙት!” አለችው። እርሱም፣ “አነጋገርሽ እንደ ሞኝ ሴት ነው፤ መልካሙን ነገር ከእግዚአብሔር ዘንድ ተቀበልን፤ ክፉውንስ አንቀበልምን? አላት።” በዚህ ሁሉ፣ ኢዮብ በንግግሩ አልበደለም።