ኢየሱስም እንዲህ አላቸው፤ “እግዚአብሔር አባታችሁ ቢሆን ኖሮ፣ እኔ ከእግዚአብሔር ወጥቼ መጥቻለሁና፣ በወደዳችሁኝ ነበር፤ እርሱ ላከኝ እንጂ በገዛ ራሴ አልመጣሁም። የምናገረውን ለምን አታስተውሉም? ምክንያቱም ቃሌን መስማት ስለማትችሉ ነው። እናንተ የአባታችሁ የዲያብሎስ ናችሁ፤ የአባታችሁንም ፍላጎት ለመፈጸም ትሻላችሁ። እርሱ ከመጀመሪያ ነፍሰ ገዳይ ነበር፤ በርሱ ዘንድ እውነት ስለሌለ በእውነት አልጸናም፤ እርሱ ሐሰተኛ፣ የሐሰትም አባት በመሆኑ ሐሰትን ሲናገር፣ የሚናገረው ከራሱ አፍልቆ ነው፤ እኔ ግን እውነት ስለምናገር አታምኑኝም! ከእናንተ ስለ ኀጢአት በማስረጃ ሊከስሰኝ የሚችል አለን? እውነት የምናገር ከሆነ፣ ለምን አታምኑኝም? ከእግዚአብሔር የሆነ እግዚአብሔር የሚለውን ይሰማል፤ እናንተ ግን ከእግዚአብሔር ስላልሆናችሁ አትሰሙም።”
ዮሐንስ 8 ያንብቡ
ያዳምጡ ዮሐንስ 8
ያጋሩ
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: ዮሐንስ 8:42-47
8 ቀናት
ክርስቲያን ከሆንክ ያለማቋረጥ በጦርነት ላይ ነህ። በአካላዊ ጉዳት ስለተጠቃህ አይደለም፣ ነገር ግን መንፈሳዊ ኃይሎች ከአምላክ ሊያርቁህ ስለሚሞክሩ ነው። አንተን ለመጠበቅ እግዚአብሔር መንፈሳዊ የጦር ትጥቅ ይሰጥሃል። ይህ የንባብ እቅድ - የእግዚአብሔር የጦር ትጥቅ ምን እንደሚመስል እና እንዴት እንደሚጠቀሙበት ያብራራል።
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
ቤት
መጽሐፍ ቅዱስ
እቅዶች
ቪዲዮዎች