በመጨረሻም የቤተ መቅደስ ጠባቂዎቹ፣ ወደ ካህናት አለቆችና ወደ ፈሪሳውያን ተመልሰው ሄዱ፤ እነርሱም ጠባቂዎቹን፣ “ለምን አላመጣችሁትም?” አሏቸው። ጠባቂዎቹም፣ “እንደዚህ ሰው፣ ከቶ ማንም ተናግሮ አያውቅም” ሲሉ መለሱ። ፈሪሳውያንም እንዲህ ሲሉ መለሱ፤ “እናንተም ተታልላችኋል ማለት ነው? ለመሆኑ ከባለሥልጣኖችና ከፈሪሳውያን በርሱ ያመነ አለ? ሕጉን የማያውቅ ይህ ሕዝብ ግን የተረገመ ነው።” ከዚህ ቀደም ወደ ኢየሱስ ሄዶ የነበረውና ከእነርሱ አንዱ የሆነው ኒቆዲሞስ እንዲህ አላቸው፤ “ሕጋችን፣ አስቀድሞ አንድን ሰው ሳይሰማና ምን እንዳደረገ ሳይረዳ ይፈርድበታልን?” እነርሱም፣ “አንተም ደግሞ ከገሊላ ነህን? ነቢይ ከገሊላ እንደማይነሣ መርምር፤ ትደርስበታለህ” ብለው መለሱለት። [
ዮሐንስ 7 ያንብቡ
ያዳምጡ ዮሐንስ 7
ያጋሩ
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: ዮሐንስ 7:45-52
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
ቤት
መጽሐፍ ቅዱስ
እቅዶች
ቪዲዮዎች