ዮሐንስ 6:22-24

ዮሐንስ 6:22-24 NASV

በማግስቱም በባሕሩ ማዶ የቀሩት ሰዎች በዚያ አንዲት ጀልባ ብቻ እንደ ነበረች ተረዱ፤ ኢየሱስ እንዳልተሳፈረና ደቀ መዛሙርቱ ብቻቸውን እንደ ሄዱም ዐወቁ። ከዚያም በኋላ፣ ሌሎች ጀልባዎች ከጥብርያዶስ ሕዝቡ ጌታ የባረከውን እንጀራ ወደ በላበት ስፍራ መጡ። ሰዎቹም፣ ኢየሱስ ወይም ደቀ መዛሙርቱ በዚያ አለመኖራቸውን እንዳወቁ፣ ኢየሱስን ፍለጋ በጀልባዎቹ ወደ ቅፍርናሆም ሄዱ።