ዮሐንስ 6:16-21

ዮሐንስ 6:16-21 NASV

በመሸም ጊዜ ደቀ መዛሙርቱ ወደ ባሕር ወረዱ፤ በጀልባውም ተሳፍረው ወደ ቅፍርናሆም ለመሻገር ተነሡ። ጊዜው መሽቶ ነበር፤ ኢየሱስም ወደ እነርሱ ገና አልመጣም ነበር። ኀይለኛ ነፋስ ይነፍስ ስለ ነበር ባሕሩ ተናወጠ። ዐምስት ወይም ስድስት ኪሎ ሜትር ያህል እንደ ቀዘፉ፣ ኢየሱስ በውሃ ላይ እየተራመደ ወደ ጀልባዋ ሲመጣ አይተው ፈሩ። እርሱ ግን፣ “እኔ ነኝ፤ አትፍሩ” አላቸው። እነርሱም እንዲሳፈር ፈለጉ፤ ጀልባዋም ወዲያውኑ ወደሚሄዱበት ዳርቻ ደረሰች።