ዮሐንስ 16:5-11

ዮሐንስ 16:5-11 NASV

“እንግዲህ ወደ ላከኝ እሄዳለሁ፤ ይሁን እንጂ ከእናንተ፣ ‘የምትሄደው የት ነው?’ ብሎ የሚጠይቀኝ የለም። ይህን በመናገሬም ልባችሁ በሐዘን ተሞልቷል፤ ነገር ግን፣ እውነት እላችኋለሁ፤ መሄዴ ይበጃችኋል። እኔ ካልሄድሁ አጽናኙ ወደ እናንተ አይመጣም፤ ከሄድሁ ግን እርሱን ወደ እናንተ እልካለሁ፤ በሚመጣበትም ጊዜ ዓለምን ስለ ኀጢአት፣ ስለ ጽድቅና ስለ ፍርድ ይወቅሣል። ስለ ኀጢአት ሲባል፣ ሰዎች በእኔ ስለማያምኑ ነው፤ ስለ ጽድቅ፣ ወደ አብ ስለምሄድና ከእንግዲህ ስለማታዩኝ ነው፤ ስለ ፍርድም፣ የዚህ ዓለም ገዥ ስለ ተፈረደበት ነው።