ዮሐንስ 13:22-25

ዮሐንስ 13:22-25 NASV

ደቀ መዛሙርቱም ማንን ማለቱ እንደ ሆነ ግራ ተጋብተው እርስ በርሳቸው ተያዩ። ከእነርሱ አንዱ፣ ኢየሱስ ይወድደው የነበረ ደቀ መዝሙር ወደ ኢየሱስ ደረት ተጠግቶ ተቀምጦ ነበር። ስምዖን ጴጥሮስም ይህን ደቀ መዝሙር በምልክት ጠቅሶ፣ “ማንን ማለቱ እንደ ሆነ ጠይቀው” አለው። እርሱም ወደ ኢየሱስ ደረት ተጠግቶ፣ “ጌታ ሆይ፤ ማን ይሆን?” ብሎ ጠየቀው።