በመጀመሪያ ቃል ነበረ፤ ቃልም ከእግዚአብሔር ጋራ ነበረ፤ ቃልም እግዚአብሔር ነበረ። እርሱም በመጀመሪያ ከእግዚአብሔር ጋራ ነበረ። ሁሉ ነገር በርሱ ተፈጥሯል፤ ከተፈጠረው ሁሉ ያለ እርሱ የተፈጠረ ምንም የለም። ሕይወት በርሱ ነበረች፤ ይህች ሕይወት የሰው ብርሃን ነበረች። ብርሃንም በጨለማ ያበራል፤ ጨለማውም አላሸነፈውም። ከእግዚአብሔር የተላከ ዮሐንስ የተባለ አንድ ሰው ነበረ። ሰዎች ሁሉ በርሱ በኩል እንዲያምኑ፣ ስለ ብርሃን ምስክር ሆኖ ለመቆም መጣ፤ ስለ ብርሃን ሊመሰክር መጣ እንጂ እርሱ ራሱ ብርሃን አልነበረም። ለሰው ሁሉ ብርሃን ሰጪ የሆነው እውነተኛው ብርሃን ወደ ዓለም እየመጣ ነበር። እርሱ በዓለም ውስጥ ነበረ፤ ዓለም የተፈጠረው በርሱ ቢሆንም እንኳ፣ ዓለም አላወቀውም። ወደ ራሱ ወገኖች መጣ፤ የገዛ ወገኖቹ ግን አልተቀበሉትም፤ ለተቀበሉትና በስሙ ላመኑት ሁሉ ግን የእግዚአብሔር ልጆች የመሆን መብት ሰጣቸው። እነዚህም ከእግዚአብሔር ተወለዱ እንጂ፣ ከደም ወይም ከሥጋ ፈቃድ ወይም ከወንድ ፈቃድ አልተወለዱም።
ዮሐንስ 1 ያንብቡ
ያዳምጡ ዮሐንስ 1
ያጋሩ
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: ዮሐንስ 1:1-13
5 ቀናት
እግዚአብሔር ራሱን በቃሉ መጽሐፍ ገልጦ ወደ እርሱ እንድንቀርብ እና ወደ መንፈሳዊ ብስለት እንድናድግ ያስታጥቀዋል። ይህ የአምስት ቀን ዕቅድ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ጽሑፎች በውደ-ሕይወታቸው እንዴት እንደሚረዱ እና ክርስቶስን ያማከለ፣ አዳኝ እና ለውጥ ሊያመጣ የሚችለውን ሊታደር ማድነቅ እንደምንችል ይዳስሳል።
7 días
Desde el principio de los tiempos, la Palabra de Dios ha restaurado corazones y mentes de manera activa: Y Dios no ha terminado aún. En este Plan especial de 7 días, celebremos el poder que transforma vidas de la Escritura observando más detenidamente cómo Dios está usando la Biblia para impactar en la historia y cambiar vidas alrededor del mundo.
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
ቤት
መጽሐፍ ቅዱስ
እቅዶች
ቪዲዮዎች