ኤርምያስ 4:1-4

ኤርምያስ 4:1-4 NASV

“እስራኤል ሆይ፤ ብትመለስ፣ ወደ እኔ ብትመለስ” ይላል እግዚአብሔር፤ “አስጸያፊ ነገሮችህን ከፊቴ ብታስወግድ፣ ባትናወጥ ብትቆምም፣ በእውነት፣ በቅንነትና በጽድቅ፣ ‘ሕያው እግዚአብሔርን!’ ብለህ ብትምል፣ አሕዛብ በርሱ ይባረካሉ፤ በርሱም ይከበራሉ።” እግዚአብሔር ለይሁዳና ለኢየሩሳሌም ሰዎች እንዲህ ይላል፤ “ዕዳሪውን መሬት ዕረሱ፤ በእሾኽም መካከል አትዝሩ። እናንተ የይሁዳ ሰዎች፣ የኢየሩሳሌምም ነዋሪዎች፤ ለእግዚአብሔር ተገረዙ፤ የልባችሁንም ሸለፈት አስወግዱ፤ አለዚያ ስለ ሠራችሁት ክፋት፣ ቍጣዬ እንደ እሳት ይንበለበላል፤ ሊገታውም የሚችል የለም።