“በማሕፀን ሳልሠራህ ዐወቅሁህ፤ ከመወለድህ በፊት ለየሁህ፤ ለሕዝቦችም ነቢይ እንድትሆን ሾምሁህ።” እኔም፣ “ጌታ እግዚአብሔር ሆይ፤ እንዴት እንደምናገር አላውቅም፤ ገና ሕፃን ልጅ ነኝና” አልሁ። እግዚአብሔር ግን እንዲህ አለኝ፤ “ ‘ገና ሕፃን ልጅ ነኝ’ አትበል፤ ወደምልክህ ሁሉ ሄደህ፣ ያዘዝሁህን ሁሉ ትናገራለህ፤ እኔ አድንህ ዘንድ ከአንተ ጋራ ነኝና አትፍራቸው” ይላል እግዚአብሔር። እግዚአብሔርም እጁን ዘርግቶ አፌን ዳሰሰና እንዲህ አለኝ፤ “እነሆ፤ ቃሌን በአፍህ አኑሬአለሁ፤ እንግዲህ፣ እንድትነቅልና እንድታፈርስ፣ እንድታጠፋና እንድትገለብጥ፣ እንድታንጽና እንድትተክል በአሕዛብና በመንግሥታት ላይ ዛሬ ሾምሁህ።”
ኤርምያስ 1 ያንብቡ
ያዳምጡ ኤርምያስ 1
ያጋሩ
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: ኤርምያስ 1:5-10
6 ቀናት
ልክ ከኤርሚያስና ከዳዊት ህይወት እንደምትመለከተው ሁሉ ዓላማህን ለመኖር፣ እግዚአብሔርን ባለህ ነገርና ባለህበት ቦታ ለማገልገል ታናሽ አይደለህም፡፡ ለዓላማህ መዘጋጀት ማለት ምን ማለት እንደሆነ እና ዓላማህን ሊያጠፉት ከሚያደፍጡ መጠበቅን ተማር፤ እንዲሁም ለአንድ ነገር ተዘጋጅ ይኽውም ትርጉም ያለውን ህይወት እና ዓለምን ሊባርክ የሚችለውን እግዚአብሔርን የሚያከብረውን ህይወት ለመኖር፡፡
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
ቤት
መጽሐፍ ቅዱስ
እቅዶች
ቪዲዮዎች