ጌዴዎን ብዙ ሚስቶች ስላገባ ሰባ ልጆች ነበሩት፤ በሴኬም የምትኖረው ቁባቱም እንደዚሁ ወንድ ልጅ ወለደችለት፤ ስሙንም አቢሜሌክ አለው። የኢዮአስ ልጅ ጌዴዎን ዕድሜ ጠግቦ ሞተ፤ በአቢዔዝራውያን ምድር ባለችው በዖፍራ፣ በአባቱ በኢዮአስ መቃብር ተቀበረ። ጌዴዎን ሞቶ ብዙም ሳይቈይ እስራኤላውያን የበኣልን አማልክት በማምለክ አመነዘሩ፤ በኣልብሪትንም አምላካቸው አደረጉ፤ በዙሪያቸው ከነበሩት ጠላቶቻቸው እጅ የታደጋቸውን እግዚአብሔር አምላካቸውን አላሰቡትም። እንዲሁም ይሩባኣል የተባለው ጌዴዎን ለእስራኤል ያደረገላቸውን በጎ ነገር ሁሉ ዐስበው ለቤተ ሰቡ ውለታ መላሽ ሆነው አልተገኙም።
መሳፍንት 8 ያንብቡ
ያዳምጡ መሳፍንት 8
ያጋሩ
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: መሳፍንት 8:30-35
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
ቤት
መጽሐፍ ቅዱስ
እቅዶች
ቪዲዮዎች