ከዚያም የጌታ ድምፅ፣ “ማንን እልካለሁ? ማንስ ይሄድልናል?” ሲል ሰማሁት። እኔም፣ “እነሆኝ፤ እኔን ላከኝ!” አልሁ። እርሱም እንዲህ አለኝ፤ “ወደዚህ ሕዝብ ሂድ፤ “ ‘መስማትን ትሰማላችሁ፤ ነገር ግን አታስተውሉም፤ ማየትንም ታያላችሁ፤ ነገር ግን ልብ አትሉም’ ብለህ ንገራቸው። የዚህን ሕዝብ ልብ አደንድን፤ ጆሯቸውን ድፈን፤ ዐይኖቻቸውንም ክደን፤ ይህ ካልሆነማ፣ በዐይናቸው አይተው፣ በጆሯቸው ሰምተው፣ በልባቸውም አስተውለው በመመለስ ይፈወሳሉ።” እኔም፣ “ጌታ ሆይ፤ ይህ የሚሆነው እስከ መቼ ነው?” አልሁት። እርሱም መልሶ እንዲህ አለኝ፤ “ከተሞች እስኪፈራርሱና የሚኖሩባቸው እስኪያጡ፣ ቤቶችም ወና እስኪሆኑና ምድርም ፈጽሞ ባድማ እስክትሆን ድረስ፤ እግዚአብሔርም ሰዎችን እስከሚያርቅ፣ ምድሪቱም ጨርሶ ባዶ እስክትሆን፣ ከዐሥር አንድ ሰው እንኳ በምድሪቱ ቢቀር፣ እርሱም ደግሞ ይጠፋል፤ ነገር ግን የኮምበልና የወርካ ዛፍ በተቈረጠ ጊዜ ጕቶ እንደሚቀር፣ ቅዱሱም ዘር እንዲሁ በምድሪቱ ጕቶ ሆኖ ይቀራል።”
ኢሳይያስ 6 ያንብቡ
ያዳምጡ ኢሳይያስ 6
ያጋሩ
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: ኢሳይያስ 6:8-13
5 ቀናት
እንደ ኢየሱስ ለመምራት ተጠርተናል። መሪነት የሚጀምረው በአንድ ሰው እንጂ በአቋም አይደለም፣ እና የመሪነት ግብ የእግዚአብሔርን ህዝብ ወደ አላማው ማንቀሳቀስ ነው። እያንዳንዱ እነዚህ ዕለታዊ ንባቦች በአመራር አውድ ውስጥ ጠንካራ መሰረት እንድትጥሉ ይረዱሃል፣ መሪ ከመሆንህ በፊት አገልጋይ እንደሆንክ እና አገልጋይ ከመሆንህ በፊት አንተ የእግዚአብሔር ተወዳጅ ልጅ እንደሆንክ ያስታውሰሃል።
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
ቤት
መጽሐፍ ቅዱስ
እቅዶች
ቪዲዮዎች