ንጉሥ ዖዝያን በሞተበት ዓመት እግዚአብሔርን ከፍ ባለና በከበረ ዙፋን ላይ ተቀምጦ አየሁት፤ የልብሱም ዘርፍ ቤተ መቅደሱን ሞልቶት ነበር። ሱራፌልም ከርሱ በላይ ቆመው ነበር፤ እያንዳንዳቸውም ስድስት ክንፍ ነበራቸው። በሁለት ክንፍ ፊታቸውን ይሸፍኑ ነበር፤ በሁለት ክንፍ እግራቸውን ይሸፍኑ ነበር፤ በሁለቱም ክንፍ ይበርሩ ነበር። እርስ በርሳቸው በመቀባበልም፣ “ቅዱስ፣ ቅዱስ፣ ቅዱስ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር፤ ምድር ሁሉ በክብሩ ተሞልታለች” ይሉ ነበር። ከድምፃቸው ጩኸት የተነሣ የመድረኩ መሠረት ተናወጠ፤ ቤተ መቅደሱም በጢስ ተሞላ። እኔም፣ “ከንፈሮቼ የረከሱብኝ ሰው ነኝ፤ የምኖረውም ከንፈሮቹ በረከሱበት ሕዝብ መካከል ነው፤ ዐይኖቼም ንጉሡን፣ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔርን አይተዋልና ጠፍቻለሁ፣ ወዮልኝ!” አልሁ። ከዚያም ከሱራፌል አንዱ፣ ከመሠዊያው ላይ የእሳት ፍም በጕጠት ወስዶ፣ ወደ እኔ እየበረረ መጣ። አፌንም በእሳቱ ነክቶ፣ “እነሆ፤ ይህ ከንፈሮችህን ነክቷል፤ በደልህ ተወግዶልሃል፤ ኀጢአትህም ተሰርዮልሃል” አለኝ። ከዚያም የጌታ ድምፅ፣ “ማንን እልካለሁ? ማንስ ይሄድልናል?” ሲል ሰማሁት። እኔም፣ “እነሆኝ፤ እኔን ላከኝ!” አልሁ። እርሱም እንዲህ አለኝ፤ “ወደዚህ ሕዝብ ሂድ፤ “ ‘መስማትን ትሰማላችሁ፤ ነገር ግን አታስተውሉም፤ ማየትንም ታያላችሁ፤ ነገር ግን ልብ አትሉም’ ብለህ ንገራቸው። የዚህን ሕዝብ ልብ አደንድን፤ ጆሯቸውን ድፈን፤ ዐይኖቻቸውንም ክደን፤ ይህ ካልሆነማ፣ በዐይናቸው አይተው፣ በጆሯቸው ሰምተው፣ በልባቸውም አስተውለው በመመለስ ይፈወሳሉ።”
ኢሳይያስ 6 ያንብቡ
ያዳምጡ ኢሳይያስ 6
ያጋሩ
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: ኢሳይያስ 6:1-10
5 ቀናት
እግዚአብሔር ራሱን በቃሉ መጽሐፍ ገልጦ ወደ እርሱ እንድንቀርብ እና ወደ መንፈሳዊ ብስለት እንድናድግ ያስታጥቀዋል። ይህ የአምስት ቀን ዕቅድ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ጽሑፎች በውደ-ሕይወታቸው እንዴት እንደሚረዱ እና ክርስቶስን ያማከለ፣ አዳኝ እና ለውጥ ሊያመጣ የሚችለውን ሊታደር ማድነቅ እንደምንችል ይዳስሳል።
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
ቤት
መጽሐፍ ቅዱስ
እቅዶች
ቪዲዮዎች