በደላችን በፊትህ በዝቷል፤ ኀጢአታችን መስክሮብናል፤ በደላችን ከእኛ አልተለየም፤ ዐመፀኝነታችንንም እናውቃለን። በእግዚአብሔር ላይ ዐምፀናል፤ ሐሰት ተናግረናል፤ አምላካችንን ከመከተል ዘወር ብለናል፤ ዐመፃንና ግፍን አውርተናል፤ ልባችን የፀነሰውን ውሸት ተናግረናል። ስለዚህ ፍትሕ ከእኛ ርቋል፤ ጽድቅም በሩቁ ቆሟል፤ እውነት በመንገድ ላይ ተሰናክሏል፤ ቅንነትም መግባት አልቻለም። እውነት የትም ቦታ አይገኝም፤ ከክፋት የሚርቅ ለጥቃት የተጋለጠ ነው። እግዚአብሔር ተመለከተ፤ ፍትሕ በመታጣቱም ዐዘነ። ማንም እንደሌለ አየ፤ ወደ እርሱ የሚማልድ ባለመኖሩ ተገረመ፤ ስለዚህ የገዛ ክንዱ ድነት አመጣለት፤ የራሱም ጽድቅ ደግፎ ያዘው። ጽድቅን እንደ ጥሩር አጠለቀ፤ የድነትን ቍር በራሱ ላይ ደፋ፤ የበቀልንም ልብስ ለበሰ፤ መጐናጸፊያ እንደሚደረብም ቅናትን ደረበ። እንደ ሥራቸው መጠን፣ ቍጣን ለባላጋራዎቹ፣ ፍዳን ለጠላቶቹ፣ እንደዚሁ ይከፍላቸዋል፤ ለደሴቶችም የእጃቸውን ይሰጣቸዋል።
ኢሳይያስ 59 ያንብቡ
ያዳምጡ ኢሳይያስ 59
ያጋሩ
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: ኢሳይያስ 59:12-18
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
ቤት
መጽሐፍ ቅዱስ
እቅዶች
ቪዲዮዎች