የተቤዠህ፣ የእስራኤል ቅዱስ፣ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “እኔ እግዚአብሔር አምላክህ፣ የሚበጅህ ምን እንደ ሆነ የማስተምርህ፣ መሄድ በሚገባህ መንገድ የምመራህ ነኝ። ትእዛዜን ሰምተህ ብቻ ቢሆን ኖሮ፣ ሰላምህ እንደ ወንዝ፣ ጽድቅህም እንደ ባሕር ሞገድ በሆነ ነበር። ዘርህ እንደ አሸዋ፣ ልጆችህ ስፍር እንደሌለው ትቢያ በሆኑ ነበር፤ ስማቸው አይወገድም፤ ከፊቴም አይጠፋም።” ከባቢሎን ውጡ፣ ከባቢሎናውያንም ሽሹ! ይህን በእልልታ አስታውቁ፤ ዐውጁት፤ እስከ ምድር ዳርቻ ድረስ ተናገሩ፤ “እግዚአብሔር ባሪያውን ያዕቆብን ተቤዥቶታል” በሉ። በምድረ በዳ ሲመራቸው አልተጠሙም ነበር፤ ውሃ ከዐለት አፈለቀላቸው፤ ዐለቱን ሰነጠቀ፤ ውሃውም በኀይል ፈልቆ ወጣ። “ለክፉዎች ሰላም የላቸውም” ይላል እግዚአብሔር።
ኢሳይያስ 48 ያንብቡ
ያዳምጡ ኢሳይያስ 48
ያጋሩ
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: ኢሳይያስ 48:17-22
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
ቤት
መጽሐፍ ቅዱስ
እቅዶች
ቪዲዮዎች