ኢሳይያስ 26:1-6

ኢሳይያስ 26:1-6 NASV

በዚያ ቀን ይህ መዝሙር በይሁዳ ምድር ይዘመራል፤ ብርቱ ከተማ አለችን፤ አምላካችን ቅጥሮቿንና ምሽጎቿን፣ ለድነት አድርጓል። በእምነቱ የጸና ጻድቅ የሆነ ሕዝብ ይገባ ዘንድ፣ በሮቿን ክፈቱ። በአንተ ላይ ታምናለችና፣ በአንተ የምትደገፈውን ነፍስ ፈጽመህ በሰላም ትጠብቃታለህ። በእግዚአብሔር ለዘላለም ታመኑ፤ ጌታ እግዚአብሔር የዘላለም ዐለት ነውና። በከፍታ የሚኖሩትን ዝቅ ዝቅ ያደርጋል፤ ከፍ ከፍ ያለችውን ከተማ ያዋርዳል፤ ወደ ምድር ይጥላታል፤ ከትቢያም ጋራ ይደባልቃታል። እግር፣ የተጨቋኞች እግር፣ የድኾች ኮቴ ይረግጣታል።