ኢሳይያስ 14:24-27

ኢሳይያስ 14:24-27 NASV

የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ብሎ ምሏል፤ “እንደ ዐቀድሁት በርግጥ ይከናወናል፤ እንደ አሰብሁትም ይሆናል። አሦርን በምድሬ ላይ አደቅቃለሁ፤ በተራራዬም ላይ እረግጠዋለሁ፤ ቀንበሩ ከሕዝቤ ላይ ይነሣል፤ ሸክሙም ከትከሻቸው ላይ ይወርዳል።” ለምድር ሁሉ የታሰበው ዕቅድ ይህ ነው፤ በአሕዛብም ሁሉ ላይ የተዘረጋው እጅ ይኸው ነው። የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ አስቧል፤ ማንስ ያግደዋል? እጁም ተዘርግቷል? ማንስ ይመልሰዋል?