ኢሳይያስ 12:4-6

ኢሳይያስ 12:4-6 NASV

በዚያ ቀን እንዲህ ትላላችሁ፤ “እግዚአብሔርን አመስግኑ፤ ስሙንም ጥሩ፤ ያደረገውንም በአሕዛብ መካከል አስታውቁ፤ ስሙ ከፍ ከፍ ማለቱንም ዐውጁ። ለእግዚአብሔር ዘምሩ፤ ታላቅ ሥራ ሠርቷልና፤ ይህም ለዓለም ሁሉ ይታወቅ። የጽዮን ሕዝብ ሆይ፤ እልል በሉ፤ በደስታም ዘምሩ፤ በመካከላችሁ ያለው የእስራኤል ቅዱስ ታላቅ ነውና።”