ኢሳይያስ 12:2-6

ኢሳይያስ 12:2-6 NASV

እነሆ፣ አምላክ ድነቴ ነው፤ እታመናለሁ፣ ደግሞም አልፈራም፤ ጌታ እግዚአብሔር ብርታቴና ጋሻዬ ነው፤ ድነቴም ሆኗል።” ከድነቴ ምንጮች ውሃ በደስታ ትቀዳላችሁ። በዚያ ቀን እንዲህ ትላላችሁ፤ “እግዚአብሔርን አመስግኑ፤ ስሙንም ጥሩ፤ ያደረገውንም በአሕዛብ መካከል አስታውቁ፤ ስሙ ከፍ ከፍ ማለቱንም ዐውጁ። ለእግዚአብሔር ዘምሩ፤ ታላቅ ሥራ ሠርቷልና፤ ይህም ለዓለም ሁሉ ይታወቅ። የጽዮን ሕዝብ ሆይ፤ እልል በሉ፤ በደስታም ዘምሩ፤ በመካከላችሁ ያለው የእስራኤል ቅዱስ ታላቅ ነውና።”