ሆሴዕ 12:2-6

ሆሴዕ 12:2-6 NASV

እግዚአብሔር በይሁዳ ላይ የሚያቀርበው ክስ አለው፤ ያዕቆብን እንደ መንገዱ ይቀጣዋል፤ እንደ ሥራውም ይከፍለዋል። በማሕፀን ሳለ የወንድሙን ተረከዝ ያዘ፤ ሙሉ ሰውም ሲሆን ከአምላክ ጋራ ታገለ። ከመልአኩም ጋራ ታገለ፤ አሸነፈውም፤ በፊቱ ሞገስን ለማግኘት አልቅሶ ለመነው፣ እርሱንም በቤቴል አገኘው፤ በዚያም ከርሱ ጋራ ተነጋገረ፤ የሰራዊት አምላክ እግዚአብሔር፣ የሚታወቅበት ስሙ እግዚአብሔር ነው። ስለዚህ ወደ አምላክህ ተመለስ፤ ፍቅርንና ፍትሕን ጠብቅ፤ ዘወትርም በአምላክህ ታመን።