እንግዲህ ዝላችሁ ተስፋ እንዳትቈርጡ፣ ከኀጢአተኞች የደረሰበትን እንዲህ ያለውን ተቃውሞ የታገሠውን እርሱን አስቡ። ከኀጢአት ጋራ ስትታገሉ ገና ደማችሁን እስከ ማፍሰስ ድረስ አልተቃወማችሁም። ልጆች እንደ መሆናችሁ እንዲህ በማለት የተናገራችሁን ማበረታቻ ቃልም ረስታችኋል፦ “ልጄ ሆይ፤ የጌታን ተግሣጽ አታቃልል፤ በሚቀጣህም ጊዜ ተስፋ አትቍረጥ፤ ምክንያቱም ጌታ የሚወድደውን ይገሥጻል፤ እንደ ልጅ የሚቀበለውንም ይቀጣል።” እግዚአብሔር እንደ ልጆቹ ይዟችኋልና የተግሣጽን ምክር ታገሡ፤ ለመሆኑ አባቱ የማይቀጣው ልጅ ማን ነው? ልጆች ሁሉ በሚቀጡበት ቅጣት ተካፋይ ካልሆናችሁ፣ ዲቃሎች እንጂ ልጆች አይደላችሁም። ከዚህም በላይ፣ እኛ ሁላችን የሚቀጡን ምድራዊ አባቶች ነበሩን፤ እናከብራቸውም ነበር። ታዲያ ለመናፍስት አባት እንዴት አብልጠን በመገዛት በሕይወት አንኖርም! አባቶቻችን መልካም መስሎ እንደ ታያቸው ለጥቂት ጊዜ ይቀጡን ነበር፤ እግዚአብሔር ግን የቅድስናው ተካፋዮች እንድንሆን ለእኛ ጥቅም ሲል ይቀጣናል። ቅጣት ሁሉ በወቅቱ የሚያሳዝን እንጂ ደስ የሚያሰኝ አይመስልም፤ በኋላ ግን ለለመዱት ሰዎች የጽድቅና የሰላም ፍሬ ያስገኝላቸዋል። ስለዚህ የዛለውን ክንዳችሁንና የደከመውን ጕልበታችሁን አበርቱ። ዐንካሳው እንዲፈወስ እንጂ የባሰውኑ እንዳያነክስ “ለእግራችሁ ቀና መንገድ አብጁ።”
ዕብራውያን 12 ያንብቡ
ያዳምጡ ዕብራውያን 12
ያጋሩ
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: ዕብራውያን 12:3-13
5 ቀናት
በአሸናፊው በክርስቶስ በኩል እግዚአብሔር ለዘለዓለም ከሀጢአትና ከሞት ነፃ አውጥቶ ጠብቆናል፤ አሁንም በዚህ በወደቀ ዓለም ይጠብቀናል፤ አንድ ቀንም ወደ ራሱ በደህና ያደርሰናል፡፡
18 ቀናት
ሐዋርያው ጳውሎስ ለአንባቢዎቹ “ወደ እግዚአብሔር መንግሥት በብዙ መከራ እንገባ ዘንድ ያስፈልገናል” (የሐዋርያት ሥራ 14:22) ይላል። የሐዋርያት ሥራን ማንበብ ወይም በዓለም ዙሪያ ካሉ ክርስቲያኖችን ምስክርነት መስማት፣ የዚህን ቃል እውነት አረጋግጠዋል። አማኞች ተቃውሞ እና ስደት ይደርስባቸዋል። ምናልባት እርሶም መከራ አጋጥሞት ይሆናል። በዚህ የንባብ እቅድ ውስጥ፣ ልናበረታታዎት እና በመከራን እንዴት መቋቋም እንደሚቻል ማስተማር እንፈልጋለን።
28 ቀናት
ባይብል ፕሮጀክት የዘወረደ ተከታታይ ትምህርቶችን ያዘጋጀው ግለሰቦች፣ ቡድኖች እንዲሁም ቤተሰቦች ዘወረደን፣ ማለትም የኢየሱስን ወደ ምድር መምጣት እንዲያከብሩ ለማነሳሳት ነው። ተስፋ፣ ሰላም፣ ሀሴት እና ፍቅር መጽሐፍ ቅዱሳዊ ትርጉማቸው ምን እንደሚመስል ተሳታፊዎች እንዲያጤኑ ለማገዝ እንዲጠቅም፣ ይህ የአራት ሳምንት የጥናት እቅድ የአኒሜሽን ቪዲዮዎችን፣ አጫጭር ማጠቃለያዎችን እና ሃሳብ ጫሪ ጥያቄዎችን አካቷል። እነዚህ አራት መንፈሳዊ እሴቶች እንዴት በኢየሱስ በኩል ወደ አለም እንደመጡ ለመረዳት፣ ይህን የጥናት እቅድ ይምረጡ።
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
ቤት
መጽሐፍ ቅዱስ
እቅዶች
ቪዲዮዎች