ዕብራውያን 1:5-9

ዕብራውያን 1:5-9 NASV

እግዚአብሔር፣ “አንተ ልጄ ነህ፤ እኔ ዛሬ ወለድሁህ፤” ወይስ ደግሞ፣ “እኔ አባት እሆነዋለሁ፤ እርሱም ልጄ ይሆናል” ያለው ከመላእክት ከቶ ለማን ነው? ደግሞም እግዚአብሔር በኵሩን ወደ ዓለም ሲያስገባ፣ “የእግዚአብሔር መላእክት ሁሉ ይስገዱለት” ይላል። ስለ መላእክትም ሲናገር፣ “መላእክቱን ነፋሳት፣ አገልጋዮቹንም የእሳት ነበልባል ያደርጋል” ይላል። ስለ ልጁ ግን እንዲህ ይላል፤ “አምላክ ሆይ፤ ዙፋንህ ከዘላለም እስከ ዘላለም ጸንቶ ይኖራል፤ የመንግሥትህ በትር የቅንነት በትር ይሆናል። ጽድቅን ወደድህ፤ ዐመፃን ጠላህ፤ ስለዚህ እግዚአብሔር አምላክህ ከባልንጀሮችህ በላይ አስቀመጠህ፣ የደስታንም ዘይት ቀባህ።”