ሐጌ 1

1
የእግዚአብሔርን ቤት ለመሥራት የተደረገ ጥሪ
1ዳርዮስ በነገሠ በሁለተኛው ዓመት፣ በስድስተኛው ወር የመጀመሪያ ቀን፣ የእግዚአብሔር ቃል በነቢዩ በሐጌ በኩል ወደ ይሁዳ ገዥ ወደ ሰላትያል ልጅ ወደ ዘሩባቤልና ወደ ሊቀ ካህናቱ ወደ ኢዮሴዴቅ ልጅ ወደ ኢያሱ#1፥1 የየሹዋ ተለዋጭ ስም ሲሆን፣ በሐጌ መጽሐፍ ውስጥ በብዛት ይገኛል። እንዲህ ሲል መጣ፤
2የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “ይህ ሕዝብ፣ ‘የእግዚአብሔር ቤት የሚሠራበት ጊዜ ገና ነው’ ይላል።”
3እግዚአብሔርም ቃል በነቢዩ በሐጌ በኩል እንዲህ ሲል መጣ፤ 4“ይህ ቤት ፈርሶ ሳለ፣ እናንተ ራሳችሁ በተዋቡ ቤቶቻችሁ ውስጥ ለመኖር ጊዜው ነውን?”
5ስለዚህ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “እስኪ መንገዳችሁን ልብ በሉ፤ 6ብዙ ዘራችሁ፤ ነገር ግን ያጨዳችሁት ጥቂት ነው። በላችሁ፤ ግን አልጠገባችሁም። ጠጣችሁ፤ ግን አልረካችሁም። ለበሳችሁ፤ ግን አልሞቃችሁም። ደመወዝን ተቀበላችሁ፤ ግን በቀዳዳ ኰረጆ የማስቀመጥ ያህል ነው።”
7የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “እስኪ መንገዳችሁን ልብ በሉ፤ 8ወደ ተራራ ውጡ፤ ዕንጨት አምጡ፤ ቤቱን ሥሩ፤ እኔም በርሱ ደስ ይለኛል፤ እከበርበታለሁም” ይላል እግዚአብሔር9የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “ብዙ ተስፋ አደረጋችሁ፤ ያገኛችሁት ግን ጥቂት ነው፤ ወደ ቤት ያስገባችሁትንም እኔ እፍ አልሁበት፤ ይህ የሆነው ለምን ይመስላችኋል? የእኔ ቤት ፈርሶ እያለ ሁላችሁም የራሳችሁን ቤት ለመሥራት ስለ ሮጣችሁ ነው፤ 10ስለዚህ በእናንተ ምክንያት ሰማያት ጠል ከለከሉ፤ ምድርም ፍሬዋን ነሣች። 11እኔም በዕርሻዎችና በተራሮች፣ በእህሉና በአዲሱ ወይን ጠጅ፣ በዘይቱና ምድር በምታፈራው ሁሉ፣ በሰውና በእንስሳ፣ በእጆቻችሁም ሥራ ላይ ድርቅ አመጣሁ።”
12ከዚህ በኋላ የሰላትያል ልጅ ዘሩባቤል፣ ሊቀ ካህናቱ የኢዮሴዴቅ ልጅ ኢያሱ፣ ከምርኮ የተረፉትም ሕዝብ የአምላካቸውን የእግዚአብሔርን ድምፅ፣ የነቢዩንም የሐጌን መልእክት ሰሙ፤ አምላካቸው እግዚአብሔር ልኮታልና። ሕዝቡም እግዚአብሔርን ፈሩ።
13ቀጥሎም የእግዚአብሔር መልእክተኛ ሐጌ፣ ይህን የእግዚአብሔርን መልእክት ለሕዝቡ እንዲህ ሲል ተናገረ፤ “እኔ ከእናንተ ጋራ ነኝ” ይላል እግዚአብሔር14ስለዚህ እግዚአብሔር የይሁዳን ገዥ፣ የሰላትያልን ልጅ የዘሩባቤልን መንፈስ፣ የሊቀ ካህናቱን የኢዮሴዴቅን ልጅ የኢያሱን መንፈስና ከምርኮ የተረፈውን ሕዝብ ሁሉ መንፈስ አነሣሣ፤ እነርሱም መጥተው የአምላካቸውን የሰራዊት ጌታ የእግዚአብሔርን ቤት መሥራት ጀመሩ። 15ይህ የሆነውም ዳርዮስ በነገሠ በሁለተኛው ዓመት፣ በስድስተኛው ወር፣ በሃያ አራተኛው ቀን ነበር።

Currently Selected:

ሐጌ 1: NASV

ማድመቅ

ያጋሩ

ኮፒ

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ