ሕዝብህን ለመታደግ፣ የቀባኸውንም ለማዳን ወጣህ፤ የክፋትን ምድር መሪ ቀጠቀጥህ፤ ከራስ ጠጕሩ እስከ እግር ጥፍሩም ዕርቃኑን አስቀረኸው። ሴላ እንደ ዐውሎ ነፋስ ሊበታትነን የመጣውን፣ ምስኪኑን በስውር በመዋጥ የሚደሰተውን፣ የሰራዊት አለቃ ራስ፣ በገዛ ጦሩ ወጋህ። ታላላቅ ውሆችን በመናጥ፣ ባሕሩን በፈረሶችህ ረገጥህ። እኔ ሰማሁ፤ ልቤም ደነገጠብኝ፤ ከንፈሬ ከድምፁ የተነሣ ተንቀጠቀጠ፤ ፍርሀት እስከ ዐጥንቴ ዘልቆ ገባ፤ እግሬም ተብረከረከ፤ ሆኖም በሚወርረን ሕዝብ ላይ እስኪመጣ ድረስ፣ የጥፋትን ቀን በትዕግሥት እጠባበቃለሁ። ምንም እንኳ የበለስ ዛፍ ባያፈራ፣ ከወይን ተክልም ፍሬ ባይገኝ፣ የወይራም ዛፍ ፍሬ ባይሰጥ፣ ዕርሻዎችም ሰብል ባይሰጡ፣ የበጎች ጕረኖ እንኳ ባዶውን ቢቀር፣ ላሞችም በበረት ውስጥ ባይገኙ፣ እኔ ግን በእግዚአብሔር ደስ ይለኛል፤ በድነቴ አምላክ ሐሤት አደርጋለሁ። ጌታ እግዚአብሔር ኀይሌ ነው፤ እግሮቼን እንደ ዋላ እግሮች ያደርጋል፤ በከፍታዎችም ላይ ያስሄደኛል።
ዕንባቆም 3 ያንብቡ
ያዳምጡ ዕንባቆም 3
ያጋሩ
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: ዕንባቆም 3:13-19
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
ቤት
መጽሐፍ ቅዱስ
እቅዶች
ቪዲዮዎች