ዘፍጥረት 9:20-27

ዘፍጥረት 9:20-27 NASV

ኖኅ ገበሬ ነበረና ወይን ተከለ፤ ከወይኑም ጠጅ ጠጥቶ ሰከረና በድንኳኑ ውስጥ ዕርቃኑን ተኛ። የከነዓን አባት ካም የአባቱን ዕርቃነ ሥጋ አየ፤ ወደ ውጭም ወጥቶ ለሁለቱ ወንድሞቹ ነገራቸው። ሴምና ያፌት ግን ልብስ ወስደው በጫንቃቸው ላይ አደረጉና የአባታቸውን ዕርቃነ ሥጋ እንዳያዩ ፊታቸውን አዙረው የኋሊት በመሄድ የአባታቸውን ዕርቃነ ሥጋ ሸፈኑ። ኖኅ ከወይን ጠጁ ስካር ሲነቃ፣ ታናሽ ልጁ ያደረገበትን ዐወቀ፤ እንዲህም አለ፤ “ከነዓን የተረገመ ይሁን፤ ለወንድሞቹም፣ የባሪያ ባሪያ ይሁን።” ደግሞም፤ “የሴም አምላክ እግዚአብሔር ይባረክ፤ ከነዓንም የሴም ባሪያ ይሁን። እግዚአብሔር የያፌትን ግዛት ያስፋ፤ ያፌት በሴም ድንኳኖች ይኑር፤ ከነዓንም የርሱ ባሪያ ይሁን” አለ።

ቪዲዮ ለ {{ዋቢ_ሰዉ}}