ዘፍጥረት 26:7-9

ዘፍጥረት 26:7-9 NASV

የዚያም አገር ሰዎች ስለ ሚስቱ በጠየቁት ጊዜ፣ “እኅቴ ናት” አለ፤ ምክንያቱም፣ “ሚስቴ ናት ብል ርብቃ ቈንጆ ስለ ሆነች፣ ያገሬው ሰዎች በርሷ ምክንያት ይገድሉኛል” በማለት ፈርቶ ነበር። ይሥሐቅ ብዙ ጊዜ በዚያ ከኖረ በኋላ፣ የፍልስጥኤም ንጉሥ አቢሜሌክ አንድ ቀን ወደ ውጭ ሲመለከት፣ ይሥሐቅ ሚስቱን ርብቃን ሲዳራት አየ። አቢሜሌክም ይሥሐቅን ጠርቶ፣ “እርሷ ሚስትህ ሆና ሳለች፣ እንዴት ‘እኅቴ ናት’ ትላለህ?” አለው። ይሥሐቅም፣ “በርሷ ሰበብ፣ ሕይወቴን እንዳላጣ ብዬ ነው” አለው።

ቪዲዮ ለ {{ዋቢ_ሰዉ}}