እግዚአብሔር በተናገረው መሠረት ሣራን ዐሰባት፤ የገባውንም ተስፋ ፈጸመላት። ሣራ ፀነሰች፤ ልክ እግዚአብሔር ባለው ጊዜ ለአብርሃም ወንድ ልጅ ወለደችለት። አብርሃም፣ ሣራ የወለደችለትን ልጅ ስሙን ይሥሐቅ አለው። አብርሃም፣ እግዚአብሔር ባዘዘው መሠረት ልጁን ይሥሐቅን በተወለደ በስምንተኛው ቀን ገረዘው። አብርሃም፣ ልጁ ይሥሐቅ ሲወለድለት፣ ዕድሜው መቶ ዓመት ነበረ። ሣራም፣ “እግዚአብሔር ሣቅ አድሎኛል፤ ስለዚህ፣ ይህን የሚሰማ ሁሉ ከእኔ ጋራ ይሥቃል” አለች። ደግሞም፣ “ለመሆኑ፣ ‘ሣራ ልጆች ታጠባለች’ ብሎ ለአብርሃም ማን ተናግሮት ያውቅ ነበር? ይኸው በስተርጅናው ወንድ ልጅ ወለድሁለት” አለች።
ዘፍጥረት 21 ያንብቡ
ያዳምጡ ዘፍጥረት 21
ያጋሩ
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: ዘፍጥረት 21:1-7
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
ቤት
መጽሐፍ ቅዱስ
እቅዶች
ቪዲዮዎች