ዘፍጥረት 18:9-12

ዘፍጥረት 18:9-12 NASV

እነርሱም አብርሃምን፣ “ሚስትህ ሣራ የት አለች?” ብለው ጠየቁት። እርሱም፣ “ድንኳን ውስጥ ናት” አላቸው። እግዚአብሔርም፣ “ጊዜው ሲደርስ በርግጥ በዚህ ጊዜ በሚቀጥለው ዓመት እመለሳለሁ፤ ሚስትህ ሣራ ወንድ ልጅ ትወልዳለች” አለው። ሣራም በዚህ ጊዜ ከበስተጀርባው ካለው ከድንኳኑ ደጃፍ ሆና ትሰማ ነበር። በዚያ ጊዜ አብርሃምና ሣራ አርጅተው፣ ዕድሜያቸው ገፍቶ ነበር፤ ሣራም ልጅ የመውለጃዋ ዕድሜ ዐልፎ ነበር። ሣራ በልቧ፣ “ካረጀሁና ጌታዬም ከደከመ በኋላ በዚህ ነገር መደሰት ይሆንልኛል?” ብላ ሣቀች።

ቪዲዮ ለ {{ዋቢ_ሰዉ}}