ሕዝቅኤል 42:15-20

ሕዝቅኤል 42:15-20 NASV

በቤተ መቅደሱ ውስጥ ያለውን ስፍራ ለክቶ ከጨረሰ በኋላ፣ በምሥራቅ በር በኩል ወደ ውጩ አወጣኝ፤ በዙሪያው ያለውንም ስፍራ ሁሉ ለካ፤ በምሥራቅ ያለውንም በመለኪያው ዘንግ ለካ፤ ዐምስት መቶ ክንድ ሆነ። ሰሜኑንም ለካ፤ በመለኪያው ዘንግ ዐምስት መቶ ክንድ ሆነ። ደቡቡንም ለካ፤ በመለኪያው ዘንግ ዐምስት መቶ ክንድ ሆነ። ከዚያም ወደ ምዕራብ ጐን ዞሮ ለካ፤ በመለኪያው ዘንግ ዐምስት መቶ ክንድ ሆነ። ስለዚህ በአራቱም ማእዘን ለካው፤ የተቀደሰውን ስፍራ ከሌላው የሚለይ በዙሪያው ግንብ ነበረ፤ የግንቡም ርዝመት ዐምስት መቶ ክንድ ሲሆን፣ ወርዱ ዐምስት መቶ ክንድ ነበር።