ዘፀአት 40:32-38

ዘፀአት 40:32-38 NASV

እግዚአብሔር ሙሴን እንዳዘዘው ወደ መገናኛው ድንኳን በገቡና ወደ መሠዊያው በቀረቡ ቍጥር ይታጠቡ ነበር። ከዚያም ሙሴ በማደሪያውና በመሠዊያው ዙሪያ አደባባዩን ተከለ፤ በአደባባዩም መግቢያ ላይ መጋረጃውን ሰቀለ፤ እንደዚህ አድርጎ ሙሴ ሥራውን ፈጸመ። ከዚያም ደመናው የመገናኛውን ድንኳን ሸፈነ፤ የእግዚአብሔርም ክብር ማደሪያውን ሞላ። ደመናው በላዩ ላይ ስለ ነበረና የእግዚአብሔርም ክብር ማደሪያውን ስለ ሞላው፣ ሙሴ ወደ መገናኛው ድንኳን መግባት አልቻለም። በእስራኤላውያን ጕዞ ሁሉ ደመናው ከማደሪያው ላይ በተነሣ ጊዜ፣ ይጓዙ ነበር፤ ደመናው ካልተነሣ ግን፣ እስከሚነሣበት ቀን ድረስ አይጓዙም ነበር። ስለዚህ በጕዟቸው ሁሉ ወቅት፣ በእስራኤል ቤት ፊት ሁሉ የእግዚአብሔር ደመና በቀን ከማደሪያው በላይ፣ በሌሊትም እሳቱ በደመናው ውስጥ ነበር።

ቪዲዮ ለ {{ዋቢ_ሰዉ}}