እግዚአብሔር ሙሴን አለው፤ “ስጦታ እንዲያመጡልኝ ለእስራኤላውያን ንገራቸው። ይሰጥ ዘንድ ልቡ ካነሣሣው ከእያንዳንዱ ሰው ስጦታን ተቀበልልኝ። “ከእነርሱ የምትቀበላቸው ስጦታዎች እነዚህ ናቸው፤ “ወርቅ፣ ብርና፣ ንሓስ፤ ሰማያዊ፣ ሐምራዊ፣ ቀይ ማግና የበፍታ ድር ልብስ፣ የፍየል ጠጕር፤ ቀይ የተነከረ የአውራ በግ ቈዳ፣ የለፋ ቈዳ፣ የግራር ዕንጨት፤ ለመብራት የወይራ ዘይት፤ ለቅብዐ ዘይቱና ለጣፋጭ መዐዛ ላለው ዕጣን የሚሆኑ ቅመሞች፤ በኤፉድና በደረት ኪስ ላይ የሚሆኑ መረግዶችና ሌሎች ዕንቍዎች። “ከዚያም መቅደስ እንዲሠሩልኝ አድርግ፤ እኔም በመካከላቸው ዐድራለሁ። ማደሪያ ድንኳኑንና በውስጡ ያለውን ዕቃ ሁሉ ልክ እኔ በማሳይህ ዕቅድ መሠረት ሥሩት።
ዘፀአት 25 ያንብቡ
ያዳምጡ ዘፀአት 25
ያጋሩ
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: ዘፀአት 25:1-9
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
ቤት
መጽሐፍ ቅዱስ
እቅዶች
ቪዲዮዎች