ዘፀአት 21:12-16

ዘፀአት 21:12-16 NASV

“ሰውን ደብድቦ የገደለ ሞት ይገባዋል። ሆኖም እግዚአብሔር ፈቅዶ ሰውየው ሳያውቅ በድንገት አድርጎት ከሆነ፣ እኔ ወደምወስነው ስፍራ ይሽሽ። አንድ ሰው በተንኰል ሆነ ብሎ ሌላውን ቢገድል፣ ከመሠዊያዬ ተወስዶ ይገደል። “አባቱን ወይም እናቱን የሚመታ ይገደል። “አንዱ ሌላውን ጠልፎ የሸጠ ወይም በተያዘ ጊዜ ከእጁ ላይ የተገኘበት ይገደል።

ቪዲዮ ለ {{ዋቢ_ሰዉ}}