ዘፀአት 2:15-21

ዘፀአት 2:15-21 NASV

ፈርዖንም ይህን በሰማ ጊዜ፣ ሙሴን ሊገድለው ፈለገ፤ ሙሴ ግን ከፈርዖን ሸሽቶ ወደ ምድያም ሄደ፤ እዚያም እንደ ደረሰ በአንድ የውሃ ጕድጓድ አጠገብ ተቀመጠ። የምድያም ካህን ሰባት ሴቶች ልጆች ነበሩት፤ እነርሱም ወደ ውሃው ጕድጓድ መጥተው የአባታቸውን በጎች ውሃ ለማጠጣት ገንዳውን ሞሉት። እረኞችም መጥተው ሴቶቹን ሲያባርሯቸው ሙሴ ከተቀመጠበት ተነሥቶ ተከላከለላቸው፤ በጎቻቸውንም አጠጣላቸው። ሴቶቹም ወደ አባታቸው ወደ ራጉኤል በተመለሱ ጊዜ፣ “ዛሬስ ያለወትሯችሁ እንዴት ፈጥናችሁ ተመለሳችሁ?” አላቸው። እነርሱም፣ “አንድ ግብጻዊ ከእረኞች እጅ አዳነን፤ እንዲያውም ውሃ ቀድቶ በጎቻችንን አጠጣልን” አሉት። አባታቸውም፣ ሴቶች ልጆቹን “የት አለ? ለምን ትታችሁት መጣችሁ? ጥሩትና ዐብሮን እንጀራ ይብላ” አላቸው። ሙሴም ከሰውየው ጋራ ለመኖር ተስማማ፤ ራጉኤልም ልጁን ሲፓራን ዳረለት።

ቪዲዮ ለ {{ዋቢ_ሰዉ}}