ዘፀአት 11:1-3

ዘፀአት 11:1-3 NASV

እግዚአብሔር ሙሴን እንዲህ አለው፤ “በፈርዖንና በግብጽ ላይ አንድ ሌላ መቅሠፍት አወርድባቸዋለሁ፤ ከዚያም በኋላ ፈርዖን ይለቅቃችኋል፤ ሲለቅቃችሁም አንዳችሁን ሳያስቀር ያስወጣችኋል። ለእስራኤል ሕዝብ፣ ለወንዶቹም ሆነ ለሴቶቹ የብርና የወርቅ ዕቃዎች ከየጎረቤቶቻቸው ስጡን ብለው እንዲወስዱ ንገራቸው።” እግዚአብሔርም እስራኤላውያን በግብጻውያን ዘንድ ሞገስ እንዲያገኙ አደረጋቸው። ሙሴም በግብጽ ምድር በፈርዖን ሹማምትና በመላው ሕዝብ ዘንድ እጅግ የተከበረ ሰው ሆነ።

ቪዲዮ ለ {{ዋቢ_ሰዉ}}