ኤፌሶን 2:4-9

ኤፌሶን 2:4-9 NASV

ነገር ግን በምሕረቱ ባለጠጋ የሆነ እግዚአብሔር ለእኛ ካለው ከታላቅ ፍቅሩ የተነሣ፣ በበደላችን ሙታን ሆነን ሳለ፣ በክርስቶስ ሕያዋን አደረገን፤ የዳናችሁት በጸጋ ነው። እግዚአብሔርም ከክርስቶስ ጋራ አስነሣን፤ በክርስቶስ ኢየሱስ በሰማያዊ ስፍራ ከርሱ ጋራ አስቀመጠን፤ ይኸውም በሚመጣው ዘመን በክርስቶስ ኢየሱስ በቸርነቱ የገለጠልንን ወደር የሌለውን የጸጋውን ባለጠግነት ያሳይ ዘንድ ነው። በእምነት፣ በጸጋ ድናችኋልና፤ ይህም የእግዚአብሔር ስጦታ ነው እንጂ ከእናንተ አይደለም፤ ማንም እንዳይመካ በሥራ አይደለም፤

ከ ኤፌሶን 2:4-9ጋር የተዛመዱ ነፃ የንባብ እቅዶች እና ምንባቦች