መክብብ 4:9-11

መክብብ 4:9-11 NASV

ለሥራቸው መልካም ውጤት ስለሚያገኙ፣ ከአንድ፣ ሁለት መሆን ይሻላል፤ አንዱ ቢወድቅ፣ ባልንጀራው ደግፎ ያነሣዋል። ቢወድቅ የሚያነሣው ረዳት የሌለው ግን፣ እንዴት አሳዛኝ ነው! ደግሞም ሁለቱ ዐብረው ቢተኙ ይሞቃቸዋል፤ ነገር ግን አንዱ ብቻውን እንዴት ሊሞቀው ይችላል?