መክብብ 4:4-6

መክብብ 4:4-6 NASV

እንዲሁም ጥረትና የሥራ መከናወን ሁሉ ሰው በባልንጀራው ላይ ካለው ቅናት እንደሚመነጭ ተመለከትሁ፤ ይህም ደግሞ ከንቱ፣ ነፋስንም እንደ መከተል ነው። ሞኝ እጁን አጣጥፎ ይቀመጣል፤ የገዛ ራሱንም ሥጋ ይበላል። በድካምና ነፋስን በመከተል ከሚገኝ ሁለት ዕፍኝ ይልቅ፣ በርጋታ የሚገኝ አንድ ዕፍኝ ይሻላል።