ከባርነት ምድር ከግብጽ ያወጣህን እግዚአብሔርን እንዳትረሳ ተጠንቀቅ! አምላክህን እግዚአብሔርን ፍራ፤ እርሱን ብቻ አገልግል፤ በስሙም ማል። በዙሪያህ ያሉ ሕዝቦች የሚያመልኳቸውን ሌሎች አማልክት አትከተል፤ ምክንያቱም በመካከልህ ያለው አምላክህ እግዚአብሔር ቀናተኛ አምላክ ስለ ሆነ፣ በአንተም ላይ ቍጣው ስለሚነድድ፣ ከምድር ገጽ ያጠፋሃል። በማሳህ እንዳደረግኸው እግዚአብሔር አምላክህን አትፈታተነው። አምላካችሁ እግዚአብሔር የሰጣችሁን ትእዛዞች፣ ምስክርነቶችና ሥርዐቶች በጥንቃቄ ጠብቁ። መልካም እንዲሆንልህና እግዚአብሔር ለአባቶችህ በመሐላ እንድትወርሳት፣ በእግዚአብሔር ፊት ተስፋ የሰጣቸውን መልካሚቱን ምድር ገብተህ ቀናና መልካም የሆነውን አድርግ፤ እግዚአብሔር በተናገረው መሠረትም ጠላቶችህን ሁሉ ከፊትህ ታስወጣለህ።
ዘዳግም 6 ያንብቡ
ያዳምጡ ዘዳግም 6
ያጋሩ
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: ዘዳግም 6:12-19
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
ቤት
መጽሐፍ ቅዱስ
እቅዶች
ቪዲዮዎች