ዘዳግም 34:1-6

ዘዳግም 34:1-6 NASV

ሙሴ ከሞዓብ ሜዳ ተነሥቶ ለኢያሪኮ ትይዩ ወደ ሆነው ፈስጋ ጫፍ፣ ወደ ናባው ተራራ ወጣ። በዚያም እግዚአብሔር ምድሪቱን ሁሉ አሳየው፤ ይኸውም ከገለዓድ እስከ ዳን፣ ንፍታሌምን ሁሉ፣ የኤፍሬምንና የምናሴን ግዛት፣ እስከ ምዕራብ ባሕር ድረስ ያለውን የይሁዳን ምድር ሁሉ፣ ኔጌብንና የዘንባባ ከተማ ከሆነችው ከኢያሪኮ ሸለቆ እስከ ዞዓር ያለውን ምድር ሁሉ ነው። ከዚያም በኋላ እግዚአብሔር ሙሴን “ለአብርሃም፣ ለይሥሐቅና ለያዕቆብ፣ ‘ለዘሮቻችሁ እሰጣለሁ’ ብዬ በመሐላ ቃል የገባሁላቸው ምድር ይህች ናት። በዐይንህ እንድታያት አድርጌአለሁ፤ ነገር ግን ወደዚያ አትሻገርም” አለው። እግዚአብሔር እንደ ተናገረው የእግዚአብሔር አገልጋይ ሙሴ በሞዓብ ምድር ሞተ። በሞዓብ ምድር በቤተ ፌጎር ፊት ለፊት ባለው ሸለቆ ቀበረው፤ ይሁን እንጂ መቃብሩ የት እንደ ሆነ እስከ ዛሬ ማንም አያውቅም።