ዘዳግም 26:5-11

ዘዳግም 26:5-11 NASV

አንተም በአምላክህ በእግዚአብሔር ፊት እንዲህ ብለህ ትናገራለህ፤ “አባቴ ዘላን ሶርያዊ ነበር፤ ከጥቂት ሰዎችም ጋራ ወደ ግብጽ ወረደ፤ በዚያም ተቀመጠ፤ ታላቅ፣ ኀያልና ቍጥሩ የበዛ ሕዝብ ሆነ። ግብጻውያን ግን ከባድ ሥራ በማሠራት አንገላቱን፤ አሠቃዩንም። ከዚያ በኋላ የአባቶቻችን አምላክ ወደ ሆነው ወደ እግዚአብሔር ጮኽን፤ እግዚአብሔርም ጩኸታችንን ሰማ፤ ጕስቍልናችንን፣ ድካማችንንና የተፈጸመብንን ግፍ ተመለከተ። ከዚህ የተነሣ እግዚአብሔር በብርቱ እጅና በተዘረጋች ክንድ፣ በታላቅ ድንጋጤ፣ በታምራዊ ምልክትና በድንቅ ከግብጽ አወጣን። ወደዚህ ስፍራ አመጣን፤ ማርና ወተት የምታፈስሰውን ይህችን ምድር ሰጠን፤ አሁንም እግዚአብሔር ሆይ፤ እነሆ፤ አንተ የሰጠኸኝን የምድሪቱን በኵራት አምጥቻለሁ።” ቅርጫቱንም በአምላክህ በእግዚአብሔር ፊት አስቀምጠው፤ በአምላክህ በእግዚአብሔር ፊት ስገድ። ከዚያም አንተ፣ ሌዋዊውና በመካከልህ የሚኖረው መጻተኛ፣ አምላክህ እግዚአብሔር ለአንተና ለቤትህ በሰጠው በጎ ነገር ሁሉ ደስ ይበላችሁ።