ይህን እየተናገረኝ ሳለ፣ ፊቴን ወደ ምድር አቀረቀርሁ፤ የምናገረውንም ዐጣሁ። ከዚያም የሰው ልጅ የሚመስል ከንፈሮቼን ዳሰሰ፤ እኔም አፌን ከፈትሁ፤ መናገርም ጀመርሁ፤ በፊቴ የነበረውንም እንዲህ አልሁት፤ “ጌታዬ ሆይ፤ ከራእዩ የተነሣ ተሠቃይቻለሁ፤ ኀይልም ዐጣሁ። ጌታዬ ሆይ፤ ጕልበቴ ከዳኝ፤ መተንፈስም አቅቶኛል፤ እኔ አገልጋይህ ከአንተ ጋራ መነጋገር እንዴት እችላለሁ?” እንደ ገናም፣ ሰው የሚመስለው ዳሰሰኝ፤ አበረታኝም። እርሱም፣ “እጅግ የተወደድህ ሰው ሆይ፤ አትፍራ፤ ሰላም ለአንተ ይሁን፤ በርታ፤ ጽና” አለኝ። እየተናገረኝም ሳለ፣ በረታሁና፣ “ጌታዬ ሆይ፤ አበርትተኸኛልና ተናገር” አልሁት። እርሱም እንዲህ አለኝ፤ “ለምን ወደ አንተ እንደ መጣሁ ታውቃለህ? የፋርስን አለቃ ለመውጋት በቶሎ እመለሳለሁ፤ እኔም ስሄድ የግሪክ አለቃ ይመጣል። አስቀድሜ ግን በእውነት መጽሐፍ ውስጥ የተጻፈውን እነግርሃለሁ፤ ከእነዚህ አለቆች ጋራ ለመዋጋት ከአለቃችሁ ከሚካኤል በቀር የሚረዳኝ የለም።”
ዳንኤል 10 ያንብቡ
ያዳምጡ ዳንኤል 10
ያጋሩ
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: ዳንኤል 10:15-21
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
ቤት
መጽሐፍ ቅዱስ
እቅዶች
ቪዲዮዎች