ዳንኤል 10:1-6

ዳንኤል 10:1-6 NASV

የፋርስ ንጉሥ ቂሮስ በነገሠ በሦስተኛው ዓመት፣ ብልጣሶር ለተባለው ዳንኤል ራእይ ታየው። መልእክቱ እውነት ነው፤ ስለ ታላቅ ጦርነትም የሚገልጽ ነበረ። መልእክቱንም ይገነዘብ ዘንድ በራእይ ማስተዋል ተሰጠው። በዚያ ጊዜ እኔ ዳንኤል ለሦስት ሳምንት አለቀስሁ፤ ሦስቱም ሳምንት እስኪፈጸም ድረስ ምርጥ ምግብ አልበላሁም፤ ሥጋም ሆነ የወይን ጠጅ ወደ አፌ አልገባም፤ ቅባትም አልተቀባሁም። በመጀመሪያው ወር በሃያ አራተኛው ቀን፣ በታላቁ በጤግሮስ ወንዝ ዳር ቆሜ፣ ቀና ብዬ ስመለከት፣ በፊቴ በፍታ የለበሰና በወገቡም ላይ የአፌዝ ወርቅ ቀበቶ የታጠቀ አንድ ሰው አየሁ። አካሉ እንደ ቢረሌ፣ ፊቱ እንደ መብረቅ፣ ዐይኖቹ እንደሚንበለበል ፋና፣ ክንዶቹና እግሮቹ እንደ ጋለ ናስ የሚያብረቀርቁ፣ ድምፁም እንደ ብዙ ሕዝብ ድምፅ ነበር።