በርሱ በኩል ለእግዚአብሔር አብ ምስጋና እያቀረባችሁ፣ በቃልም ሆነ በተግባር የምታደርጉትን ሁሉ በጌታ በኢየሱስ ስም አድርጉት። ሚስቶች ሆይ፤ በጌታ ዘንድ ተገቢ በመሆኑ ለባሎቻችሁ ተገዙ። ባሎች ሆይ፤ ሚስቶቻችሁን ውደዱ፤ መራራም አትሁኑባቸው። ልጆች ሆይ፤ ይህ ጌታን ደስ የሚያሰኝ በመሆኑ በሁሉም ነገር ለወላጆቻችሁ ታዘዙ። አባቶች ሆይ፤ ተስፋ እንዳይቈርጡ ልጆቻችሁን አታስመርሯቸው። ባሮች ሆይ፤ ለታይታ ሰውን እንደሚያስደስቱት ሳይሆን፣ በቅን ልብ ጌታን በመፍራት ለምድራዊ ጌቶቻችሁ በሁሉ ነገር ታዘዙ። የምታደርጉትን ሁሉ ለሰው ሳይሆን ለጌታ እንደምታደርጉት ቈጥራችሁ በሙሉ ልባችሁ አድርጉት፤ ከጌታ ዘንድ እንደ ብድራት የምትቀበሉት ርስት እንዳለ ታውቃላችሁና፤ የምታገለግሉት ጌታ ክርስቶስን ነው።
ቈላስይስ 3 ያንብቡ
ያዳምጡ ቈላስይስ 3
ያጋሩ
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: ቈላስይስ 3:17-24
4 ቀናት
ይህ የአራት ቀናት ዕቅድ ጳውሎስ ወደ ቆላስይስ ሰዎች የፃፈውን ደብዳቤ ይዳስሳል፤ ይኸውም ዓለማትን የፈጠረውና የሰውን ልጅ የታደገው ከሁሉ በላይና ለሁሉ የሚበቃው ኢየሱስ መሆኑን በማስታወስ የሀሰት ትምህርቶችን በመሞገት ነው፡፡ ጳወሎስ ጨምሮም ስለ ቤተሰብ ግንኙነት፣ ፀሎት፣ ቅዱስ አኗኗር እና በፍቅር መታሰር ምን እንደሆነ ተግባራዊ ጥበብን ይሰጣል፡፡
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
ቤት
መጽሐፍ ቅዱስ
እቅዶች
ቪዲዮዎች