እግዚአብሔርም ሙላቱ ሁሉ በርሱ ይሆን ዘንድ ወድዷልና፤ በመስቀሉ ላይ በፈሰሰው ደሙ ሰላምን በማድረግ፣ በምድርም ሆነ በሰማይም ያለውን ነገር ሁሉ በርሱ በኩል ከራሱ ጋራ አስታረቀ። ከክፉ ባሕርያችሁ የተነሣ ቀድሞ ከእግዚአብሔር የተለያችሁ በዐሳባችሁም ጠላቶች ነበራችሁ። አሁን ግን ነቀፋና እንከን አልባ ቅዱስ አድርጎ በርሱ ፊት ሊያቀርባችሁ፣ በክርስቶስ ሥጋ በሞቱ በኩል አስታረቃችሁ፤
ቈላስይስ 1 ያንብቡ
ያዳምጡ ቈላስይስ 1
ያጋሩ
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: ቈላስይስ 1:19-22
4 ቀናት
ይህ የአራት ቀናት ዕቅድ ጳውሎስ ወደ ቆላስይስ ሰዎች የፃፈውን ደብዳቤ ይዳስሳል፤ ይኸውም ዓለማትን የፈጠረውና የሰውን ልጅ የታደገው ከሁሉ በላይና ለሁሉ የሚበቃው ኢየሱስ መሆኑን በማስታወስ የሀሰት ትምህርቶችን በመሞገት ነው፡፡ ጳወሎስ ጨምሮም ስለ ቤተሰብ ግንኙነት፣ ፀሎት፣ ቅዱስ አኗኗር እና በፍቅር መታሰር ምን እንደሆነ ተግባራዊ ጥበብን ይሰጣል፡፡
28 ቀናት
ባይብል ፕሮጀክት የዘወረደ ተከታታይ ትምህርቶችን ያዘጋጀው ግለሰቦች፣ ቡድኖች እንዲሁም ቤተሰቦች ዘወረደን፣ ማለትም የኢየሱስን ወደ ምድር መምጣት እንዲያከብሩ ለማነሳሳት ነው። ተስፋ፣ ሰላም፣ ሀሴት እና ፍቅር መጽሐፍ ቅዱሳዊ ትርጉማቸው ምን እንደሚመስል ተሳታፊዎች እንዲያጤኑ ለማገዝ እንዲጠቅም፣ ይህ የአራት ሳምንት የጥናት እቅድ የአኒሜሽን ቪዲዮዎችን፣ አጫጭር ማጠቃለያዎችን እና ሃሳብ ጫሪ ጥያቄዎችን አካቷል። እነዚህ አራት መንፈሳዊ እሴቶች እንዴት በኢየሱስ በኩል ወደ አለም እንደመጡ ለመረዳት፣ ይህን የጥናት እቅድ ይምረጡ።
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
ቤት
መጽሐፍ ቅዱስ
እቅዶች
ቪዲዮዎች