እናንተ በሰማርያ ተራራ የምትኖሩ የባሳን ላሞች፤ ድኾችን የምትጨቍኑና ችግረኞችን የምታስጨንቁ፣ ባሎቻችሁንም፣ “መጠጥ አቅርቡልን” የምትሉ ሴቶች ይህን ቃል ስሙ፤ ጌታ እግዚአብሔር በቅድስናው እንዲህ ሲል ምሏል፤ “እነሆ፤ በመንጠቆ ተይዛችሁ የምትወሰዱበት ትሩፋናችሁ እንኳ፣ በዓሣ መንጠቆ የሚወሰድበት ጊዜ ይመጣል። እያንዳንዳችሁ በቅጥሩ በተነደለው መሽሎኪያ ወደ ሬማንም ትጣላላችሁ፤” ይላል እግዚአብሔር። “ወደ ቤቴል ሂዱና ኀጢአትን ሥሩ፤ ወደ ጌልገላም ሂዱና ኀጢአትን አብዙ፤ በየማለዳው መሥዋዕቶቻችሁን፣ በየሦስቱ ዓመት ዐሥራታችሁን አቅርቡ። እርሾ ያለበትን እንጀራ የምስጋና መሥዋዕት አድርጋችሁ አቅርቡ፤ የበጎ ፈቃድ ስጦታችሁን አሳውቁ፤ እናንተ የእስራኤል ልጆች የምትወድዱት ይህን ነውና፤” ይላል ጌታ እግዚአብሔር።
አሞጽ 4 ያንብቡ
ያዳምጡ አሞጽ 4
ያጋሩ
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: አሞጽ 4:1-5
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
ቤት
መጽሐፍ ቅዱስ
እቅዶች
ቪዲዮዎች