አሞጽ 3:12-15

አሞጽ 3:12-15 NASV

እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “እረኛ ከአንበሳ መንጋጋ፣ ሁለት የእግር ዐጥንት ወይም የጆሮ ቍራጭ እንደሚያድን፣ እንዲሁም በሰማርያ በዐልጋቸው ጫፍ ላይ፣ በደማስቆም በምንጣፋቸው ላይ የተቀመጡ፣ እስራኤላውያን ይድናሉ።” “ይህን ስሙ፤ በያዕቆብም ቤት ላይ መስክሩ” ይላል የሰራዊት አምላክ ጌታ እግዚአብሔር። “እስራኤልን ስለ ኀጢአቷ በምቀጣበት ቀን፣ የቤቴልን መሠዊያዎች አፈርሳለሁ፤ የመሠዊያው ቀንዶች ይቈረጣሉ፤ ወደ ምድርም ይወድቃሉ። የክረምቱን ቤት፣ ከበጋው ቤት ጋራ እመታለሁ፤ በዝኆን ጥርስ ያጌጡ ቤቶችም ይደመሰሳሉ፤ ታላላቅ አዳራሾችም ይፈርሳሉ፤” ይላል እግዚአብሔር።