ሐዋርያት ሥራ 9:36-37

ሐዋርያት ሥራ 9:36-37 NASV

በኢዮጴ ጣቢታ የተባለች አንዲት ደቀ መዝሙር ነበረች፤ የስሟም ትርጓሜ ዶርቃ ማለት ነው። እርሷም ዘወትር በትጋት በጎ ነገር እያደረገችና ድኾችን እየረዳች ትኖር ነበር። በዚያ ጊዜም ታምማ ሞተች፤ ሰዎችም አስከሬኗን ዐጥበው በሰገነት ላይ ባለው ክፍል አስቀመጡት።