2 ጢሞቴዎስ 2:11-13

2 ጢሞቴዎስ 2:11-13 NASV

እንዲህ የሚለው ቃል የታመነ ነው፤ ከርሱ ጋራ ከሞትን፣ ከርሱ ጋራ ደግሞ በሕይወት እንኖራለን። ብንጸና፣ ከርሱ ጋራ ደግሞ እንነግሣለን። ብንክደው፣ እርሱ ደግሞ ይክደናል፤ ታማኞች ሆነን ባንገኝ፣ እርሱ ታማኝ እንደ ሆነ ይኖራል፤ ራሱን መካድ አይችልምና።