2 ተሰሎንቄ 3:6-12

2 ተሰሎንቄ 3:6-12 NASV

ወንድሞች ሆይ፤ ያለ ሥርዐት ከሚመላለስ እና ከእኛ በተቀበላችሁት ትምህርት መሠረት ከማይኖር ወንድም እንድትርቁ በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም እናዝዛችኋለን፤ የእኛን ምሳሌ እንዴት መከተል እንደሚገባችሁ እናንተ ራሳችሁ ታውቃላችሁና። ከእናንተ ጋራ በነበርንበት ጊዜ ሥራ ፈቶች አልነበርንም፤ ደግሞም የማንንም እንጀራ በነጻ አልበላንም፤ ነገር ግን ከእናንተ በአንዳችሁም ላይ ሸክም እንዳንሆን ሌሊትና ቀን እንደክምና እንሠራ ነበር፤ ይህን ያደረግነው ምሳሌነታችንን እንድትከተሉ ብለን እንጂ የሚያስፈልገንን ነገር ከእናንተ ለማግኘት ሥልጣን ሳይኖረን ቀርቶ አይደለም። ከእናንተ ጋራ በነበርንበት ጊዜ፣ “ሊሠራ የማይወድድ አይብላ” ብለን ይህን ትእዛዝ ሰጥተናችሁ ነበርና። ከእናንተ አንዳንዶች ያለ ሥርዐት የሚመላለሱ እንደ ሆኑ ሰምተናል፤ እነርሱም ያለ ሥራ እየዞሩ በሰው ጕዳይ ጣልቃ የሚገቡ ናቸው። እንደዚህ ያሉ ሰዎች ተግተው ሥራቸውን እንዲሠሩና እንጀራቸውን እንዲበሉ በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም እናዝዛቸዋለን፤ እንመክራቸዋለንም።